latest news

latest news (16)

“በጎነት ለአብሮነት!” በሚል መርህ የብሔራዊ በጎ ፍቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ሥልጠና ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡ “እንኳን በደህና መጣችሁ!” በማለት ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት  የአርሲ  ዩኒቨርሲቲ  የአስተዳደር ልማትና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሜሮን ረጉ

በንግግራቸው ወጣቶች አገር ተረካቢዎች በመሆናችሁ በአገር ግንባታው በንቃት በመሳተፍ አገራችንን ከበለጸጉት አገሮች ተርታ ለማሰለፍ እና ሰላሟን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች በንቃት በመሳተፍ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ ለመወጣት ራሳችሁን ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም ሰልጣኞቹ የመጡበትን ዓላማ ባለመዘንጋት የሚሰጠውን ሥልጠና በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበው አርሲ ዩኒቨርሲቲ በሥልጠናው ላይ በሚቆዩባቸው ቀናት አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው እና ከጎናቸው እንደሚቆም ገልጸዋል፡፡

      የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ለሁሉም የሥልጠናው ተሳታፊዎች ከማእከል በቬርቹዋል ባስተላለፉት መልዕክት ሥልጠናው በተለያዩ ርእሶች ላይ እንደሚሰጥ በመግለጽ እንደዚህ አይነቱ ለወጣቶች የሚሰጠው ሥልጠና ወጣቶች በአገር ግንባታው ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የብሔራዊ በጎ ፍቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ሥልጠና ለ45 ቀናት በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞቹ ከሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የመጡ ናቸው፡፡

በዶ/ር ደሴ አሰፋ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግቢ ዉበት ዳይሬክቶሬት የሚመራ አሥራ ሁለት አባላት የያዘ የልዑካን ቡድን ታህሣሥ 19 ቀን 2013 ዓ. ም በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አካሄዷል፡፡ በዚሁ መሠረት አርሲ ዩኒቨርሲቲ በማካሄድ ላይ የሚገኘውን የተለያዩ ፕሮጄክቶችን በግብርና እና አካባቢ ሳይንስ፣  በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በዩኒቨሲቲው ዋና ግቢ በመዘዋወር ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም የእንስሳት እርባታ፣ የICT መሠረት ልማቶችን የአሰላ ቲቺንግና ሪፌራል ሆስፒታል እና በዋናው ግቢ በመካሄድ ላይ የሚገኙትን ዘመናዊ የመማሪዎች ክፍሎች፣ ቤተ መጽሓፍት፣ የተማሪዎች ማደሪያ ሕንጻዎች እና የመመገቢያ አዳራሾች ጉብኝት ከማካሄዳቸውም በላይ በየክፍሉ ከሚገኙት ሠራተኞች ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርጓል፡፡ ከጉብኝቱም በኋላ የልዑካን ቡድኑ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን በጉብኝቱ ወቅት በተመለከቱዋቸው ሥራዎች እጅግ መደነቃቸውን በመግለጽ አርሲ ዩኒቨርሲቲ በተመሠረተ ጥቂት አመታት ውስጥ ተጨባጭ ተግባሮች በማከናወኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮችም በበኩላቸው አንጋፋው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ቡድን በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት በማካሄዱ አመስግነው በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚካሄዱት እንደዚህ አይነት  ጉብኝቶች ትስስር ከመፍጠር በዘለለ የልምድ ልውውጥን በማዳበር የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልዑካን በአጠቃላይ በጉብኝቱ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው  የአርሲ ዩኒቨርሲቲም በቅርብ ቀናት በባህር ዳር በመገኘት ጉብኝት እንዲያደርግ ጥሪ  አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም የአርሲ ዩኒቨርሲቲ  የICT ዳይሬክቶሬት  እና  እና በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የግቢ ውበት ላይ አስደናቂ ለውጥ ያመጡት የአነስተኛ እና ጥቃቂን ኅብረት ሥራ ማኅበራት ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉና የአጭር ጊዜ ሥልጠና እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ በመጨረሻም አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለባህር ዳር ልዑካን ቡድኑ አባላት የማስታወሻ ሥጦታ አበርክቷል፡፡

Arsi University and Sun chon National University are working on dairy project entitled “Improving Productivity of Dairy Farmers by Supporting Dairy Technology and Infrastructure”.

The university has imported 3,000 (Three Thousand) straws of Holstein Semen from two bulls (GENTLEMAN 208HO 10293 and CROWN 208HO 00540) which wasdonated by the South Korean Government through the project “Improving Productivity of Dairy Farmers by Supporting Dairy Technology and Infrastructure” to improve the dairy farmers productivity. The imported semen will used to improve the productivity of dairy cattle in Arsi university dairy farm and the neighboring community.

Arsi University BENEFIT-REALISE Cluster conducted Advisory council centred workshop on 22, December 2020 in Asella, Arsi. The workshop aims at exchanging information on project output and institutionalization of technologies that had been introduced into project mandate with advisors and the key stakeholders.

BENEFIT-REALISE is a three years project (2018 – 2020). Dr. Abebe Megersa, Arsi University BENEFIT-REALISE Cluster manager, presents objectives of the workshop and project progress summary to the participans. The discussion was conducted on the reports by the key stakeholders and participants of the workshop. Currently, Arsi University BENEFIT-REALISE works in three zones of the regional state of Oromia.

Wednesday, 16 December 2020 14:35

ዜና እረፍት

ዶ/ር ከድር ባቲ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ነባር የአካዳሚክ አባል ነበሩ፡፡ ዶ/ር ከድር ባቲ ባደረባቸው ሕመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ታህሳስ 6/2013 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለዶ/ር ከድር ባቲ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡ 

አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት አካሄደ፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሰበብ ከመጋቢት አጋማሽ 2012 ዓ. ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመጀመር አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ መሰረት ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት መልሶ ሲከፈት ሊኖሩ የሚችሉ ለውጦችን በማስገንዘብ ተገቢ የሆኑ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ማስቀጠል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ከተማሪዎችና ከተማሪዎች ጋር ግንኙነት ካላቸው የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር ለሁለት ቀናት  ውይይት አድርጓል፡፡ ተማሪዎች ለወራት ከዩኒቨርሲቲው ርቀው በመቆየታቸው ወደ ትምህርት ሲመለሱ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን የሥነ ልቡና ተጽእኖ ማስወገድ  በሚችሉባቸው ዘዴዎች፣ ስለኮቪድ-19 ምንነትና ወረርሽኙን ለመከላከል ሊወሰዱ ስለሚኖርባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች፣ እንዲሁም በወረርሽኙ ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት መከተል ስላለባቸው አሰራሮች፣  መመሪያዎች፣ ግዴታዎች እና በመሳሰሉት ርዕሶች ላይ በዘርፉ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ገለጻ ተደርጓል፡፡

ውይይቱን የመሩት ዶ/ር ቃሲም ኪሞ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዛሬም በመጨመር ላይ ቢገኝም ቫይረሱን እየተከላከልን የተቋረጠውን የገጽ ለገጽ ትምህርት የወረርሽኙን ስርጭት የማያባብሱ የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን በመጠቀም እንደገና ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ለስኬቱ ሁሉም የየበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር ሜሮን ረጉ የአስተዳደር ልማትና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ተማሪዎችን ለመቀበል የተማሪዎች ማደሪያ ሕንፃዎችና ክፍሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ ቤተ መጽሓፍት፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ከእጅ ንኪኪ ነጻ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎች በተገቢ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን ገልጸው አስፈላጊ የሆኑ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ክልከላዎች፣ ግዴታዎችንና መመሪያዎችን በማክበር የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ትምህርቱን መቀጠል እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

በ2012 ዓ. ም ተመራቂ የነበሩና የፊት ለፊት ትምህርት በመቋረጡ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው የነበሩ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት ቀርበው በመመዝገባቸው የተቋረጠው ትምህርት ሰኞ ታህሣሥ 5 ቀን 2013 ዓ. ም ይጀመራል፡፡

Yuunivarsiitiin Arsii Haala Barnoota Addaan Cite Itti Fufu Irratti Marii Gaggeesse

Yuunivarsiitiin Arsii Barnoota sababa tamsaa’ina Koovid-19n bara 2012 addaan citee itti fufsiisuf barattoota bara darbe eebbifamuun irra tureef waamicha dabarseen barattoonni qaaman argamuun galmaa’anii jiru. Haaluma kanaan barnoonni addaan citee ture yoo eegale jijjiirrama mul’achuu danda’u ilaalchisee hubachiisun of-eeggannoo taasisuudhan haala barnoonni eeggalamu irratti barsiisota, barattoota, fi hojjattoota bulchiinsaa kan barattootan walitti dhufeenya qaban waliin mariin guyyaa lamaaf adeemsisameera.  Barattoonni ji’oota saddeetii ol Yuunivarsiiticha irraa fagaatanii waan turaniif, yoo barnootatti deebi’an dhiibbaa gama xiinsamuutiin qunnamuu danda’u haala ofirraa ittisuu itti danda’an, maalummaa koovid-19, qajeelfamoota, dhooggawwani fi tarkaanfiwwan of-eeggannoo taasifamuu qaban irratti ogeessotaan ibsi kennameefii jira.

Marii kanarratti kan argaman Doktor Qaasim Kimoo, Itti aanaa Pirezidaantii dhimmoota Akaadamikii, tamsaa’inni Koovid-19 hardhallee dabalaa jiraatullee of-eeggannoo barbaachisan godhuun barnoota jalqabuun barbaachisaa ta’uu ibsanii jiru. Dabalataanis Yuunivarsiitichi qajeelfama jiru irratti hundaa’un qophii gahaa taasisuu dabalanii ibsanii jiru. Doktor Meeron Regguu, Itti aantuu Pirezidaantii Bulchiinsa Misooma fi Dhimma Barattootaa gama isaanitiin manneen kitaabbilee, laaboraatoorii, manneen nyaataa, kutaaleen barnoota fi manneen bulmaata barattootaa duursan haala qajeelfamaatiin qophaa’uu isaanii ibsanii jiru. Dabalataanis iddoowwan harka itti dhiqatan tuttuqaa harkaatirraa bilisa haala ta’een qophaa’uu ibsanii jiru. Walumaagalatti Yuunivarsiitichi barattoota isaa simachuuf qophii barbaachisaa ta’an xummuuruu isaa ibsanii jiru.

Yuunivarsiitin Arsii Muddee Guyyaa 5 bara 2013 barnoota jalqabuun, guyyoota 45niif itti fufuun ni xummura.

Sunday, 29 November 2020 14:40

እንኳን ደስ አላችሁ!

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ከሃዲውንና ዘራፊውን የትህነግ ጁንታ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በመደምሰስ መቐለ ከተማን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ባስመዘገበው አንጸባራቂ ድል የተሰማውን ታላቅ ደስታ እየገለጸ በሁሉም ዘርፍ ከመከላከያው ሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ ያልተቆጠበ ድጋፍ ሲያደርግ ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብና ነፃነት ለተጎናጸፈው የመቐለ ከተማ ነዋሪ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ይላል፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ከአገር መከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ምንጊዜም በምንም  የማይናወጽ ጽኑ አቋሙን እየገለጸ ስግብግቡ ጁንታ ያፈረሳቸውን የመሰረተ ልማት አውታሮች መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረትና በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረት አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

                                                    አርሲ ዩኒቨርሲቲ

                                         Baga Gammaddan!

Yuunivarsiitiin Arsii Raayyan Ittisa Biyyaa gantuuwwanii fi hattuuwwan Juuntaa “ABUT” guutumaa guututti barbadeessuudhaan magaala MAQALEE to’achuu isaatiin gammachuu itti dhaga’ame ibsaa Baga Gammaddan! Baga Waliinuu Gammadne! Jedha. Yuunivarsiitiin Arsii gara fuunduraatis gama maraanuu Raayyaa Ittisa Biyyaa cinaa hiriirun deeggarsa barbaachisaa ta’e hundaa godhuuf qophii ta’uu isaat ibsa! Ammas irra deebinee BAGA GAMMADDAN! BAGA GAMMADNE jedha!!!

                                          Yuunivarsiitii Arsii

አርሲዩኒቨርሲቲተማሪዎቹንአስመረቀ፡፡

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ. ም በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ሚኒስትሮች፣ የዞንና የክልል ባለሥልጣኖች፣የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የተመራቂዎች ቤተሰቦች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት አስመርቋል፡፡

በዚሁ መሠረት የጤና  ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን 40 ወንድና 20 ሴት በአጠቃላይ 60 የሕክምና ዶክተሮችን አስመርቋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ ኮሌጆች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 1064 ተማሪዎች በማስትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በኮቪድ-19 ምክንያት ጥቂት የማስትሬት ዲግሪ ተመራቂዎች ብቻ በአዳራሹ የተገኙ ሲሆን ሌሎች በያሉበት ተመርቀዋል፡፡

በምረቃው ስነ ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር  ሚኒስትርዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ባደረጉት ንግግር አርሲ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት ከነባሮቹ ተርታ የሚያሰልፈው ነው ብለዋል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተመራቂዎች ኅብረተሰባቸውን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ ባሰሙት ንግግር ዩኒቨርሲቲው ከአካባቢው የመስተዳድርና የሰላምና ፀጥታ አካላት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ከኅብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራቱ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎቱም ለማኅበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታያላቸው ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰው በጤና ዘርፍም ከውጭ ካገኛቸው የሕክምና ቁሳቁሶች መካከል 50% ለጤና ተቋማት መስጠቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Yuunivarsiitiin Arsii BarattootaEebbisiise

Yunivarsiitich barattoota ogummaa adda addaatiin barsiisaa ture Sadaasa Guyyaa 12 bara 2013 galma Yuunivarsiitichaatti haala hoo’adhaan eebbisiss jira. Haaluma kanaan koollajjiin Saayinsii Fayyaa Doktoroota 60, dhiira 40 fi dubara 20, eebbisiisee jira. Akkasumas barattoonni koollajjii gara garaa keessatti barataaturan 1064 digirii maastireetineebbisamanii jiru.

Sirna eebbaa barattootaa kana irratti keessummoonni Ministeera Saayinsii fi Barnoota  Ol’aana, Ministeera Fayyaa, Biiroo Fayyaa Oromiyaa, fi Bulchiinsa Zoonii Arsii Bahaa irraa dhufan argamanii jiru.

Haaluma kanaan Doktor Saamu’eel Kiflee, Ministeera De’eettaa Ministeera Saayinsii fi Barnoota ol’aanaa haasawa taasisaniin eebbifamtoonni biyyaa fi hawaasa isaanii ciminnaan akka tajaajilan yaadachiisu dhaan, ciminna Yuunivarsiitichaa dinqisiifatanii jiru.

Doktor Darajjee Dhugumaa, gama isaanitiin eebbifamtoonni yoo hojiitti bobban haalli jiru mijaawaa ta’uu baatullee ogummaa isaanitiin hawaasa akka tajaajilan dhaamanii jiru.

Pirezidaantiin Yuunivarsiitii Arsii Doktor Dhugumaa Addunyaa, Yuunivarsiitichi qaamota adda addaa naannoo Yuunivarsiitichaatt iargaman waliin qindoominaan waan hojjatuuf bu’aan qabatamaan argamuu isaa ibsanii jiru. Dabalataanis tajaajila hawaasummaatin Yuunivarsiitichi qabatamaan bu’uraalee misooma diriirsun tajaajilaa irra oolchuu ibsuun alatti gara fuunduraatis hojiiwwan kana fakkaatan akka hojjatu ibsanii jiru.

የአለማችን የጤና ስጋት የሆነው ኮቪድ-19 በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም በቂ መተዳደሪያ በሌላቸው፣ በአነስተኛ ስራዎች ላይ በተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በአቅመ ደካሞችና የእድሜ ባለጸጎች ላይ ዘርፈ ብዙ ተጽእኖ ማስከተሉ ይታወቃል፡፡

የበሽታው ስርጭት ዛሬም በመጨመር ላይ ቢገኝም አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ በተወሰነው መሰረት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች መሄድ ጀምረዋል፡፡  በዚሁ መሰረት በደማቸው ውስጥ ቫይረሱ ያለባቸውና ድጋፍ የሚፈልጉ ተማሪዎች በትምህርት መሳሪያዎች እጦት ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በማሰብ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የኤችይቪ-ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ለ400 ተማሪዎች የአልባሳት፣ የደብተር፣ የእስክርቢቶና የእርሳስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ ድጋፉን ያደረገው ከዞኑ የቀይ መስቀል ማህበርና ከቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመተባበር ከተለያዩ ወገኖች በማሰባሰብ ነው፡፡

 

(For applicants interested in admission for Regular/Extension)
Arsi University would like to invite competent applicants for the postgraduate program in Food Science and Technology for 2013 E.C/2021 G.C both in Regular and Extension/weakened programs in Asella Campus.
Admission Requirements
• Applicants for admission to the MSc program should have at least a bachelor's degree or its equivalent in food science, food science and postharvest technology, food engineering, human nutrition, postharvest management, postharvest technology recognized higher learning institutions.
• Students from, horticulture, plant science, animal science and other agricultural fields, biology, chemistry shall take bridge courses from undergraduate program as per the recommendation of the department academic council. Applicants must pass written entrance exams and fully satisfy the academic rules and regulation of the University.
• The appropriateness of the candidature for admission to the MSc program in FST will be determined by the Department Academic Committee.
• The admission of students shall abide with Arsi University legislation academic rules and regulations.
• Applicant from academic institution and who want to present with letter of Sponsorship can download a sponsorship letter from www.arsiun.edu.et and have stamp of the organization
• Cost of registration and tuition fee rate will be according to the Arsi University payment system for PG
• For detail information Please contact selected PG coordinators:
1. Dr. Samuel Mezemir (PhD and Ass. professor of Food Biotechnology in Arsi University), and Coordinator for University-Industry Linkage, Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
2. Dr. Meron Regu (PhD and Assistant prof. of Food and Nutrition, Arsi University) and Vice-president of the Arsi University. Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
3. Jemal Mohammed (Assistant Prof. of Food Science and Nutrition) and Associate director of Publication director Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. Tel: +251-911-267281 or +251-938188750 or +251912684008
Note
 Lab has occupied with instruments from simple (proximate analysis) to advanced analysis (UV-Vis, HPLC, and AAS)  Arsi University (FSPT) had signed memorandum of Understanding with Weihenstephan-Triesdorf University of Applied Sciences, Germany

Page 1 of 2